የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ አረፉ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ እንደተቻለው ፕሬዝዳንቱ በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው የቆዩ ቢሆንም ትናንት ሌሊት አርፈዋል።

ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን በ1917 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወልደዋል ።

በልጅነታቸ  ወቅት  የቤተ ክህነት  ትምህርት የተከታታሉ ሲሆን  ከ1926 ዓ.ም ጀምሮ  የዘመናዊ ትምህርትን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብተው እስከ ጣልያን ወረራ ድረስ ተከታትለዋል።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ከ1994 እስከ 2006 ዓም ድረስ ለ12 ዓመታት ያህል  የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር  በመሆን  አገልግለዋል  ።  

የቀድሞ ፕሬዚደንት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን መንግሥት ጀምሮ የፓርላማ አባል በመሆን አገርና ህዝብንም አገልግለዋል ።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት የኦሮምኛ፣ አማርኛ፣አፋርኛ ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን  ይናግራሉ ።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት  የአምስት ልጆች አባት ናቸው ።

ዋልታ  ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ህይወት ማለፍ ምክንያት  ጥልቅ ሃዘን  ለተሰማቸው  ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው  መጽናናትን ይመኛል ።