አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ የክብር ዶክትሬት መሥጠቱን አስታወቀ

 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በገዳ  ሥርዓት ላይ  ጥልቅ  ምርምርና ጥናት  ላደረጉት ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ የክብር ዶክትሬት  መሥጠቱን  አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትናንትናው ዕለት በተካሄደ  ሥነ ሥርዓት  ለፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ በገዳ ሥርዓት ላይ ላደረጉት ጥናት የክብር ዶክትሬትታቸውን ተበርክቶላቸዋል።

በዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ሥነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሌሌች  የሚመለከታቸው አካላት  እንዲሁም የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ምሁራን ተገኝተዋል።

ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ በገዳ ሥርዓት ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የገዳ ሥርዓትን ለዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ  ቀላል የማይባል  አስተዋጽኦ ማድረጋቸውም  ተገልጿል ።

ፕሮፌሰር አስመሮም በገዳ ሥርዓትን  በተመለከተ  የጻፉት መጽሐፍት “Gada: Three Approaches to the Study of African Society እና Oromo Democracy : An Indigenous African Political System”  በሚል  ርዕስ  የተዘጋጁ ናቸው ።