የሳዑዲ ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የሳዑዲ አረቢያ  ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ  በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት ምክንያት  የተሰማቸውን ሀዘን  ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።             

ንጉሱ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በላኩት መልዕክት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል። 

ንጉሱ  በራሳቸውና በሳዑዲ አረቢያ ህዝብ ስም በላኩት መልዕክት እንደገለጹት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን በመመኘት ከልብ ማዘናቸውን አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት ምክንያት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ ላይ  ይገኛሉ።

አምባሳደሮቹ የድሮው ጦር ኃይሎች በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የቀድሞው የፕሬዚዳንት የመኖሪያ ቤት በመገኘት ነው ሀዘናቸውን  እየገለጹ ነው

በውጭ አገራት  የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችም በተመሳሳይ ሀዘናቸውን በቀድሞ ፕሬዚደንት  ምክንያት  የተሰማቸውን ሃዘን በመገልጽ ላይ ናቸው ።

እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ የቻይና፣ ከፖርቹጋል፣ ጃፓን፣ ኔዘርላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ አሜሪካ፣ ራሽያ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ህንድ፣ ጀርመን፣ ካናዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኒጀር፣ ፊንላንድና ፍልስጤምን ጨምሮ በርካታ አምባሳደሮች በቀድሞው ፕሬዚዳንት መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የሀዘን መግለፃ መዝገብ ላይ ሀዘናቸውን የሚገልጽ ጽሑፍ አስፍረዋል።

አምባሳደሮቹ በዚሁ መልዕክታቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ከወጣትነት ጀምሮ ህዝባቸውንና አገራቸውን ከልብ  በማገልገል  የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የተወጡ  መሆናቸውን ገልጸዋል ።