አምባሳደር ረድዋን ሁሴን ወደ ኤርትራ ያቀናውን የኢትዮጵያ ሀኪሞች ቡድንን ተቀበሉ

በኤርትራ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕከተኛና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ወደ ኤርትራ ያቀናውን የኢትዮጵያ የሃኪሞች ቡድን አሥመራ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።  

አምባሳደሩ ቡድኑን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር እንዲህ ዓይነቱ በጎ ተግባር ከሰብዓዊ አገልግሎቱ ባሻጋር የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ሁለንተናዊ ግንኙነት በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።

ሰላሳ ዘጠኝ አባላትን የያዘው የሀኪሞች ቡድን ለሁለት ወራት በኤርትራ በመቆየት የተለያዩ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)