ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ መሥጠት ከጀመረች በኋላ በርካታ አፍሪካዉያን እየገቡ ነው

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ መሥጠት ከጀመረች በኋላ በርካታ አፍሪካዉያን ወደ ሃገሪቷ  እየገቡ መሆኑን የአየር ኬላዎች የኢሚግሬሽን ማስተባባሪያ መመሪያ አስታወቀ ።

የአየር ኬላዎች ኢሚግሬሽን ማስተባበሪያ መመሪያ ኃላፊ አቶ አይክፋዉ ጎሳዮ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ መሥጠት ከጀመረች  ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ 20 ሺ አፍሪካዉያን  ወደ አገሪቷ ገብተዋል፡፡

አዲሱ አሠራር ቀልጣፋና ፈጣን ለተገልጋዮች ምቹ ለማድረግ የተለያዩ አሠራሮች ተዘርግተዉ  አገልግሎት እየተሠጠ እንደሆነም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

አብዛኛዉ የአፍሪካ ሀገራት ክሬዲት ካርድ ባለመጠቀማቸዉ ምክንያት እንደሚቸገሩና ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን የሚችለዉ ሶፍትዌር መተግባሪያ ጥቅም ላይ እንዲውል  በማድረግ  ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ 

ከሌሎች አገሮች አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ ኤምባሲዎች የሚገኙ በመሆኑ  የመዳረሻ ቪዛ አሠራሩ  ተገቢ የሆነ የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጠናክር መሆኑም አክለዉ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም  በተጨማሪም የቱሪዝም ማስፋፋት እና የዉጭ ምንዛሬ ላይ በተፈለገዉ መልኩ እየተሠራበት ነዉ ብለዋል፡፡

አዲስ የተጀመረውን የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት በሁለት መንገድ የመጠቀም አማራጭ  መኖሩንምየመምሪያው ኃላፊ ገልፀዋል፡፡