ሚኒስቴሩ ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ተጓዦች የኢቦላ ምርመራ መደረጉን አስታወቀ

 በ10ኛው የኢቦላ ሥርጭት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ተጓዦች የኢቦላ ምርመራ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በትዊተር ገፃቸው እንደገለጹት፥ የኢቦላ ቫይረስ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ ሀይል ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ተጓዦች ላይ በተለያዩ መግቢያ ጣቢያዎች በቫይረሱ ያለመያዛቸውን የማረጋገጥ ሥራ እየሠራ ነው።

ግብረ ሀይሉ ይህንን ሥራውን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አራት ቦታዎች፣ በ21 የኢትዮጵያ ወሰን አካቢዎች፣ በድሬዳዋ፣ መቐለ እና ባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሁሉም የኢቦላ ቫይረስ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በቀን በአማካይ 30 ሺህ ተጓዦች ላይ ምርመራ መደረጉንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።