የምርምርና የጥናት ውጤቶችን መንግስት ሊደግፍና ክትትል ሊያደርግ ይገባል ተባለ

የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የምርምርና የጥናት ውጤቶችን መንግስት ሊደግፍና ክትትል ሊያደርግ እንደሚገባ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ምሁራን አጥኝዎች ገለጹ፡፡

በሚሊዮኖች በሚቆጠር ገንዘብ በትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች የማህበረሰቡን ችግር አጥጋቢ በሆነ መልኩ እየፈቱ አለመሆኑን የገለጹት ምሁራን አጥኝዎቹን ከመጥቀም ውጪ መሬት ላይ የሚታይ ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ታከለ ታደሰ ለጥናትና ምርምር ተግባራዊነት ተቋማቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ሲያዘጋጅም ሆነ የትኩረት መስኮችን ይፋ ሲያደርግ ህዝቡ ማወቅ የሚገባ ቢሆንም ህዝቡ እንደማያውቅ ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪዎች በራሱ እንደሚሰራና ለህዝቡ ጥቅም ቅድሚያ እንደማይሰጥ የተናገሩት ዶክተር ታከለ ህዝብ ከሚከፍለው ግብር የሚገኘው ገንዘብ ለህዝብ ጥቅም መዋል እንደሚገባ እና  አሳስበዋል፡፡

በዩኒቨርስተው የሚካሄዱ ምርምሮችም በአብዛኛው የህዝቡንና የልማት ፍላጎትን መሰረት ያላደረጉ ከመሆኑም ባሻገር የምርምር ፖሊስ ዳካማና መንግስትና በየደረጃው ያሉ ፖሊሲና ስትራቴጂ የሚነድፉ አካላት ተናበው የመሥራት ሁኔታ ደካማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ አሸናፊ አበበን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እንደገለጹት ብዙ ምሁራን ምርምር እንደሚሰሩና ምርምሮቹን በኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች በሚደረጉ ዓመታዊ ኮንፌረንሶች ይፋ ከመደረግ ውጭ በማህበረሰብ ዘንድ ለውጥ ሲያመጣ አይታይም፡፡