ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በውጭ ፖሊሲ ትግበራ ምርጥ ውጤት በማስመዝገብ በፎሬን ፖሊሲ ልዩ ዕትም እውቅና ከተሠጣቸው 10 ዓለም አቀፍ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል ።
ፎሬን ፖሊሲ ልዩ ዕትም በመከላከያናበፀጥታ ዘርፍ ምርጥ ብሎ የመረጣቸው ከዓመት ባነሰ የሥልጣን ዘመናቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ስላደረጉት አስተዋጽኦ ነው ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ በኢትዮጵያበኤርትራ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር በማድረጋቸውም ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል ንግድም ዳግም እንዲጀመር ማስቻላቸውን ጽፏል ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ በኢትዮጵያውያን ከመከፋፈል ይልቅ አንድ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሠጥተው እየሠሩ መሆናቸውንም ጭምር መጽሔቱ አትቷል ።
ጠቅላይ ሚንስትሩም ብዙ ቁጥር ካለው የኦሮሞ ህዝብ በመውጣታቸውም ለወደፊቱ ይሳካላቸዋል ተብሎም እንደሚጠበቅ መፅሔቱ ጠቁሟል ።