በባህር ዳር ከተማ የእሳት አደጋ ደረሰ

በባህርዳር ከተማ በተለምዶ ቀበሌ 5 በሚባለው አካባቢ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በርካታ ቤቶችን ማውደሙ ተገለጸ።

የባህርዳር ከተማ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምክትል ኮማንደር አሻግሬ ይገዝ እንደተናገሩት፥ ቃጠሎው መጠነ ሰፊ ስለነበረ በፍጥነት መቆጣጠር አልተቻለም።

ነዋሪዎች ደግሞ እሳቱ በተነሳበት ወቅት የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች በፍጥነት በአካባቢው ባለመገኘታቸው ለአደጋው መባባስ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ምክትል ኮማንደሩ በበኩላቸው መዘግት ቢኖርም የእሳት ቃጠሎው ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ መነሳቱን ጠቅሰው ከ20 ደቂቃዎች በኋላ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በአካባቢው መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።

አያይዘውም በአደጋው ሳቢያ የወደመውን ንብረት ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።  (ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ)