በአዲስ አበባ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ ቁስቋም በሚባል አካባቢ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪየህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ተገለፀ።

ግንባታው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ትምህርት ቤቶችን፣ የህጻናትና ሴቶች ድጋፍ ሰጪ ማዕከላትን ለማስፋፋት የተያዘው ዕቅድ አካል ነው ተብሏል፡፡።  

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለህጻናት ማሳደጊያ ማዕከሉ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በዚሁ ወቅት ወይዘሮ ዝናሽ እንደተናገሩት ማዕከሉ ለዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎትና ልማት ማህበር የህጻናት ማሳደጊያ የሚበረከት ነው።

ባለፈው ገና በዓል ዋዜማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ኮተቤ የሚገኘውን ይህንኑ የህጻናት ማሳደጊያ መጎብኘታቸው ይታወሳል።