የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ 559 ተማሪዎችን አስመረቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን አካዳሚ ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን 559 ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተገኝተዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 40ዎቹ ፓይለቶች፣ 58 ቴክኒሻን እና 123ቱ ደግሞ ሆስተስ ናቸው።

እንዲሁም 286 የሚሆኑት ደግሞ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች ሲሆኑ 52 የሚሆኑት ደግሞ የምግብ ዝግጅት ባለሙያ ናቸው ተብሏል።(ምንጭ:-ኤፍቢሲ)