ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የክበበ ጸሀይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎበኙ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የክበበ ጸሀይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎበኙ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በጉብንታቸው ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያደርገውን የግል ጥረት በማቀናጀት ለከፍተኛ ውጤት መትጋት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከሉ የሚያከናውናቸው ተግባራት ደስ የሚያሰኙ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ የግል ጥረቶቻችንን ከደመርናቸው ከፍተኛ ተግባራትን መፈጸም እንደምንችል የሚያሳይም ነው ብለዋል።

በ1956 የተመሰረተው ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት 200 የሚደርሱ ወላጅ አልባ እና አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ተቀብሎ በመንከባከብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ መኖሪያ ቤታቸውን በመስጠታቸው ስራውን የጀመረው ክበበ ጸሀይ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል በተለያየ ምክንያት ወላጅ አልባ የሆኑ ህፃናትን ዘጠኝ አመት እስኪሞላቸው ድረስ በማሳደግ ወደ ኮልፌ ህጻናት ማሳደጊያዎች ይልካቸዋል።

በማዕከሉ ካሉት ህጻናት መካከል 50 የሚሆኑት በተቋም ድጋፍ የሚያድጉ ናቸው ነው የተባለው፡፡ (ምንጭ፡-የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት)