ለፋሲካ በዓል የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጅት ተጠናቋል – ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመጪዉ የፋሲካ በዓል የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የፋሲካ በአልን አስመልክቶ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል የፀጥታ አካሉ ለሚያደርገዉ ድንገተኛ ፍተሻ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግና ማንኛዉንም ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሲመለከት በቅርብ ላለዉ የፀጥታ አካል ማሳወቅ እንዳለበትም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው አስታዉቀዋል፡፡

በበዓል ወቅት የሚኖረዉን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ የራሱን ደህንነት ለማስጠበቅ ከፀጥታ አካሉ ጋር በጋራ መስራት እንዳለበት የገለፁት ኮሚሽነሩ፣ ለመላዉ የእምነቱ ተከታዮች የመልካም በዓል ምኞታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡