የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

የፋሲካ በዓል በመላው ሀገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለሊቱን የተለያዩ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች ተከናውነዋል።

የትንሳዔን በአል ስናከብር የተቸገሩ እና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ የሀይማኖት አባቶች አሳስበዋል።