ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከዩኔስኮ ጄኔራል ዳይሬክተር ኡድሪ አዘላይ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) ጄኔራል ዳይሬክተር ኡድሪ አዘላይ ጋር ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ማዕከል ለኢትዮጵያ ያለው አጋርነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ለኢትዮጵያ ያለውን አጋርነት በተጠናና በተጠናከረ መንገድ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጄኔራል ዳይሬክተሯ በበኩላቸው ዩኔስኮ በተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎቹ አማካይነት በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡