የአእምሮ ንብረት አካዳሚ ለመክፈት ቅድመ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው ተባለ

የአእምሮ ንብረት አካዳሚ ለመክፈት ቅድመ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው ተባለ፡፡

የአለም አእምሮአዊ ንብረት ቀን “ለወርቅ እንትጋ፣ የአእምሯዊ ንብርትና ስፖርት” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት አገልግሎቱን ለማስፋት ከተለያዩ ከሀገር ዉስጥና ከዉጭ ሀገሮች ጋር በጋራ በመስራት እና የአለም አቀፍ ስምምነቶች አባል በመሆን እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ተቋሙ የአእምሮ ንብረት አካዳሚን ለመክፈት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ነው የኢንስትቲዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሉ ሞሲሳ የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት አዘጋጅነት በተካሄደው አዉደርዕይ ምርቶቻቸዉን በንግድ ፈቃድ ስም ያስመዘገቡ የፈጠራ ስራ ባለቤቶች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

ተሳታፊ የፈጠራ ስራ ባለቤቶችም የተለያዩ ችግር ፈቺ ናቸዉ ያሏቸዉን የፈጠራ ስራዎቻቸዉን በእለቱ በአዉደርዕይ አቅርበዋል፡፡

የፈጠራ ስራ ባለቤቶቹ ስራዎቻቸዉን ከሚፈልጉት አካላት ጋር ለመገናኘት አዉደርዕይው መዘጋጀቱ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውና ለተሻለ ስራ እንደሚያነሳቸው ተናግረዋል፡፡