በሳኡዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 1 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን ታራሚዎች በምህረት ተለቀቁ

በሳኡዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 1 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን የህግ ታራሚዎች በምህረት ተለቀቁ፡፡

የሳኡዲ አረቢያ መንግሰት የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የረጂም ጊዜ ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ 1 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን የህግ ታራሚዎች ነው በምህረት የለቀቀው፡፡

በተጨማሪም አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸው በ75 በመቶ እንደሚቀንስላቸው የአገሪቱ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

በምህረት ከተፈቱት መካከል 300 ያክሉ ዛሬ ሌሊት ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡

(ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)