ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢፍጣር እራት ጋበዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢፍጣር እራት ጋብዘው ለቅዱስ ረመዳን ወር ያላቸውን መልካም ምኞት ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢፍጣር እራት ንግግራቸዉ እንደ ገለጹት የሰላም፣ የአንድነት፣ የይቅርታ፣ የመስጠትና የዕርቅ እሴቶች የረመዳን መገለጫ ናቸው።

እነዚህ የመልካም እሴቶች ወር ከወር እንዲቀጥሉ ዑለማዎች ተግተው እንደሚያስተምሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

በረመዳን ወቅት የሚደረገዉን የውስጣዊ ጽዳት በውጭም ለመድገም የሚቀጥለዉ እሑድ ጠዋት ሁሉም ሰዉ ወጥቶ አካባቢውን እንዲያጸዳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት