የመጀመሪያው የማህበራዊ ጥበቃ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የመጀመሪያው አገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ጉባኤ በመንግስታቱ ድርጅት የኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ  እየተካሄደ ነው፡፡  

በጉባኤዉ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት መንግስት ማህበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ የማህበራዊ ደህንነት ዋስትና ፓሊሲ እና ስትራቴጂ አውጥቶ ተግባራዊ አድርጓል፤ ይሁን እንጂ ስኬቶች ቢኖሩም ማህበራዊ ችግሮችን መፍታት እንዳልተቻለ አክለዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት ሁሉም አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሰዊድን አምባሳደር ቶቢያን ፒተርሰን በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ መንግስት የማህበራዊ ጥበቃ ፓሊሲ እንደሚያደንቁ ጠቅሰዉ፣ የስዊድን መንግስት ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ባልደረባ ዶክተር ማይክል ሳምሶን ደግሞ የኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚ እድገት የማህበራዊ ጥበቃን ያማከለ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የማህበራዊ ጥበቃ ባለፉት አስር አመታት በአለም በሶስት እጥፍ ማደጉ ታውቋል፡፡