የኦሮሚያ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ

የኦሮሚያ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ከክልሉ የተለያዩ ከተሞች እና ዞኖች ከሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ከተውጣጡ ከ600 በላይ የጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የመድረኩ ዋነኛ አላማ በክልሉ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ግልጽ ውይይት በማካሄድ ዘርፉን ማጠናከር የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በክልሉ በጤናው ዘርፍ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የዳሰሰ ጽሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በጤናው ዘርፍ ያሉ የመሰረተ ልማት ክፍተቶችን መሙላት፤ የሆስፒታሎችን ደረጃ ማሻሻልና፤ የህክምና ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያም ውይይት ተካሂዷል፡፤

ውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በነገው እለት እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡