የፊታችን እሁድ በሚካሄደውን የፅዳት ዘመቻ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ቤቱን እና አካባቢውን እንዲያፀዳ ጥሪ ቀረበ

የፊታችን እሁድ በሚካሄደውን የፅዳት ዘመቻ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤቱን እና አካባቢውን እንዲያፀዳ የኢትዮጵያ ኡለማዎች ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት ቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ቆሻሻ የድህነት እና የውርደት ምልክት መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ቤቱን እና አካባቢውን እንዲያፀዳ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም በወንዞች አካባ የሚኖሩ ሰዎች ወንዞቹን ከብክለት እንዲጠብቁት ጠይቀዋል፡፡

በየመንገዱ የሚጣሉ ተረፈምርቶች አካባቢን ከማቆሸሽ በዘለለ ለነዋሪም ደህንነት ስጋት በመሆናቸው መንገዶችን ከቆሻሻ ልንጠብቅ ይገባልም ብለዋል፡፡

ከውጫዊ ንፅሕና ይልቅ ውስጣዊ ንፅሕና ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በሸሪዓው በግልፅ ተቀምጧል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ልባችንን ንፁህ በማድረግና ውስጣችንን ከመጥፎ ሃሳብ ልናፀዳ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውስጡ ቆሽሾ አካሉ ቢጸዳ ዋጋ የለውም ያሉት ቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጅ ኡመር የእርስ በእርስ ወዳጅነትን ማጠናከርና ውስጣችንን ከመጥፎ ነገር ማጽዳት አለብን ብለዋል፡፡