‘ገበታ ለሸገር’ የእራት ምሽት ተካሄደ

‘ገበታ ለሸገር’ የእራት ምሽት ተካሄደ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ቀዳማዊ እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ታድመዋል።

እንዲሁም ከ200 በላይ ግለሰቦች፣ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ድርጅቶች እና ተቋማት በፕሮግራሙ ለመታደም እና አሻራቸውን ለማኖር መቀመጫ ቦታ በመግዛት በእራት ምሽቱ ተገኝተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ የተለያዩ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ለሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

‘ገበታ ለሸገር’ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የአዲስ አበባን ወንዞች ዳርቻዎችን እና ሌሎች ተያያዥ መናፈሻዎችን ለማልማት ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት ለመደገፍ ገንዘብ ለማሳሰብ የተዘጋጀ ነው።

ሸገርን ማስዋብ ፕሮጅክት በሚል የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ከተማዋን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ፥ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በሶስት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።