በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልኡክ ወደ ጅቡቲ አቀና

በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ በማለዳው ወደ ጅቡቲ አቅንቷል።

ልዑኩ ወደ ጅቡቲ ያቀናው በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ-ህይወትን ተከትሎ በቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው ተብሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብዱልቃድር አህመድ ካሚል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ በሁለቱ አገራት መካከል የተጠናከረ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ ልማት እና ሰላም እንዲዳብር በሰጡት ታሪካዊ አመራር ይታወቃሉ።

የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆናቸውም በስፋት ይነገርላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ በታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ-ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በኢፌዴሪ መንግሥት ስም አስተላልፈዋል። መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ነው፡፡