የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የምስጋናና የአንድነት ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው

የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የምስጋናና የአንድነት ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

ከእስልምና ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ስታዩ የነበሩ ችግሮች ተቀርፎ ለውጥ በመምጣቱ ምክንያት ነው ፕሮግራሙ የተዘጋጀው፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር ዐብይ አህመድን ጨምሮ በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለታየው ለውጥ አስዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ምስጋና ይቀርባል ተብሏል፡፡

ለውጡ በሁሉም ከተሞችና ክልሎች መልዕክት ይተላለፋልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ ለ10 ሺህ ሰዎች ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡