በሰዓት 80ሺህ ዳቦዎች የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሰዓት 80ሺህ ዳቦዎች የሚያመርተው እና መቶ ግራም ዳቦ በ75 ሳንቲም ለሚያቀርብ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው ከ4-6 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡

በከተማ ውስጥ ያለውን የዳቦ አቅርቦት ከፍ የሚያደርገው እና የዋጋ ንረቱን የሚያረጋጋው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ግንባታው ሲጠናቀቅ አንድ ዳቦ በ75 ሳንቲም ለህብረተሰቡ ያቀርባል፡፡

የመሠረተ ድንጋይ በማኖር ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር ከግል ባለሃብቱ ጋር በመተባበር ለህብረተሰቡ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን በዝቅተኛ ዋጋ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

በሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግንባታ የሚከናወነው ይህ የዳቦ ማምረቻ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለበርካታ የአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል መረጃዉ ያገኘነዉ ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤት ነዉ ፡፡