የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት የመደወላቡና ደሎመና ወረዳዎችን የልማት ሥራዎች እየጎበኙ ነው

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች ተገኝተው የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በመደወላቡ ወረዳ የተገነባውን የመደወላቡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በደሎመና ለሚገነባው የመስኖ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ታውቋል።

በምክትል ፕሬዚዳንቱ የመሰረተ ልማት ጉብኝት ላይ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (የኦዲፒ) ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ተመልክቷል።

በተጨማሪም የኦሮሚያ ብሮድካስቲግ ኔትወርክ (ኦ.ቢ.ኤን ) የባሌ ኤፍኤም ሬድዮና ቴሌቪዥን ስርጭት የሚሆን ስቱዲዮ ለመገንባት በባሌ ሮቤ ከተማ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

አቶ ሽመልስ በትናንትናው ዕለት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በባሌ ሮቤ ከተማ ከሕብረተሰቡ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል መረጃዉ የኢዜአ ነዉ።