የክረምት ወቅት የመንገድ ችግሮችን ለመፍታት የቅድመ መከላከል ሥራ ማከናወኑን ባለስልጣኑ ገለጸ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በአዲስ አበባ የክረምት ወቅት ሲገባ የሚያጋጥሙትን የመንገድ ብልሽትና ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች መዘጋት ችግሮች ለመፍታት ከ100 በላይ መንገዶችን በመለየት የቅድመ መከላከል ሥራ ማከናወኑን ገለፀ፡፡

የቱቦዎች ፈሳሽ ማስወገጃዎች ጠረጋና ጥገና በጀሞ፣ ኃይሌ ጋርመንት፣ መገናኛ፣ ቃሊቲ፣ አዲሱ ገበያ፣ ኮተቤና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች መከናወናቸዉን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጥኡማይ ወልደገብርኤል ተናገሩ፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች የ46 ኪሎሜትር መልሶ ግንባታ፣ 50 ኪሎሜትር ጥገናና ማሻሻልና 100 ኪሎሜትር የቱቦና ፍሳሽ ጠረጋ ተከናዉኗል፡፡

በክረምቱ የቅድመ መካላከል ስራም 80 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አቶ ጥኡማይ ተናግረዋል፡፡

ህብረተስቡና የሚመለከታቸዉ የመሰረተ ልማት ተቋማት የድርሻቸዉን እንዲወጡ ኃላፊዉ አሳስበዋል፡፡