ዳኞች ለውዝፍ የክስ መዝገቦች በክረምት ወራት እልባት እንዲሰጡ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

ዳኞች ለበርካታ አመታት እየንተንከባለሉ የመጡ ውዝፍ የክስ መዝገቦችን በክረምቱ የእረፍት ሰአታቸው እልባት እንዲሰጡ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው በጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ እና  በፌዴራልና ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች መካከል ነው፡፡

ስምምነቱ በመደበኛው የስራ ጊዜ እልባት ያላገኙ ውዝፍ የክስ መዝገቦች እልባት እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ ለፍትህ ስርአቱ ማደግ ፋይዳ እንደሚኖረውም ነው የተመላከተው፡፡

በባለፈው አመት ክረምት በተሰራው ውዝፍ መዛግብቶችን እልባት የመስጠት ተግባር ወደ 23 ሺህ የሚጠጉ መዝገቦች መሰራታቸውን የጃስቲስ ፎር ኦል ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ ገልጸዋል፡፡

በዚህኛው የክረምት ወቅት ደግሞ ከ20 ሺህ እስከ 30 ሺህ የሚጠጉ መዝገቦች እልባት ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል፡፡