የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤዎች ምዕመናንን በማሳተፍ 7 ሺህ ችግኞችን ተከሉ

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምዕመናንን በማሳተፍ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ በሚገኘው ስፍራ ላይ 7 ሺህ ችግኞችን ዛሬ ተክለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው መርሀ ግብር የተሳተፉ ምዕመናን እንደገለጹት ችግኝ ተከላው ወደ ትውልዶች የሚተላለፍ ተግባር ሆኖ ሊቀጥል ይገባል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ሐምሌ 22/ 2011 ዓ.ም በተጠራው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንዲሳተፉም ለምዕመናኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተያዘው የክረምት ወቅት 4 ቢሊየን ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፣ አስካሁን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ታውቋል፡፡