ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ አመራሮችና አባላት ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ አመራሮችና አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱም በዋናነት የጥራት ሽልማት ድርጅት በሀገሪቱ የምርትና አገልግሎት አሰጣጥ በማሳደግ በኩል እየተጫወተ ያለውን ተግባር በተመለከተ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንቷም እየተሰራ ባለው የአገልግሎት ሰጪና አምራች ተቋማት ጥራታቸውን እንዲያሻሽሉ ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም መንግስት ለተቋሙ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ የጥራት ድርጅቶች የበላይ ጠባቂ ሲሆኑ፣ ድርጅቱ ባለፉት ስድስት አመታት በምርትና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትን አወዳድሮ ሲሸልም ቆይተዋል፡፡ ለሰባተኛ ጊዜም ሽልማቱን ለማካሄድ የተወዳዳሪ ተቋማትን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል፡፡