ፍርድ ቤቱ ስድስት ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ትዕዛዝ ሰጠ

በቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ መዝገብ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ስድስት ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የፌደራሉ ከፈተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

በተጨማሪም በአድራሻቸው ተፈልገው ያልተገኙ ሌሎች አምስት ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው አቃቤህግ ጠይቋል፡፡

መጥሪያ ላልደረሳቸው 23 ተከሳሾች መጥሪያ ለማድረስ የሚያስችል በቂ ጊዜ እንዲሰጠው አመልክቷል፡፡

ችሎቱ በአቃቤህግ ማመልከቻ ላይ ተገቢ ነው የሚለውን ትዕዛዝ ለመስጠት ለሀምሌ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በዛሬው እለት መቃወሚያ ባስገቡ ተከሳሾች ጉዳይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም የችሎቱ አንድ ዳኛ በእክል ምክንያት በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ብይኑን ለመስጠት ለሀምሌ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

እነ አቶ አብዲ መሃመድ ከሀምሌ 28/2010 ዓ.ም ጀምሮ በሶማሌ ክልል እና በጅግጅጋ ከተማ ዘርንና ሀይማኖትን ለይቶ በተፈፀመው ጥቃት መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡