የአማራና የሶማሌን ሕዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክር መድረክ በባህር ዳር ሊካሄድ ነው

የአማራና የሶማሌን ሕዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ እንደሚካሄድ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ እንደገለጹት የሁለቱን ሕዝቦች አንድነት ለማጠናከርና ለማሳደግ የተዘጋጀው መድረክ ሐምሌ 14 ቀን 2011 በከተማዋ ይከናወናል።

 ኢዜአ እንደዘገበው በመድረኩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ 100 የሚደርሱ የጎሳ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራንና ሌሎችም ይሳተፋሉ ብለዋል።

መድረኩ ለዘመናት ተዋዶ፣ ተፋቅሮና እርስ በእርሱ ተረዳድተው የኖሩትን ሕዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር ያስችላል ተብሎ እምነት እንደተጣለበትም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድርና የከተማ አስተዳደር መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።