የኢፌዴሪ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ተማሪዎችና አመራሮች በሱሉልታ ችግኝ ተከሉ

የተቋሙ ተማሪዎችና አመራሮች ሱሉልታ በሚገኘው የተቋሙ ቅጥር ግቢ ነው ችግኞች የተከሉት፡፡
ተማሪዎችና አመራሩ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ለመንከባከብ መዘጋጀታቸውን ለዋልታ ቴሌቭዥን ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በታቀደበት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በንቃት እንደሚሳተፉም ነው የተናገሩት፡፡
የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አመራሮች በበኩላቸው መንግስት ለአረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ  የሰጠውን ትኩረት ተቋሙ ይሰጣል፤በቀጣይም የአካባቢ ጥበቃና የችግኝ ተከላ ስራዎችም በስፋት ይሰራሉ ነው ያሉት፡፡
በችግኝ ተከላው ከ300 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡