ለህግ የበላይነት መከበር ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት ተጠቆመ

የፍትህ እኩልነትን ለማረጋገጥ የህግ የበላይነትን የማክበርና የማስከብር ሃላፊነትን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

መሰረቱን ህዝብ ያደረገ የፍትህ ስርዓት ለማፈን የፌዴራል የፍትህና ህግ መምሪያ እና ስልጠና ተቋም ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በሀገር አቀፍ ለውጡን የሚደግፍ እና የህዝብን እኩልነት የሚያረጋግጥ የፍትህ ስርዓት እንዲኖር የዘርፉ ተቋማት የህግ የበላይነትን ዋና ዓላማቸዉ አድርገው መስራትም አለባቸው ብሏል የስልጠና ተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር፡፡

ስልጠናው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤህግ ከሆላንዱ በህግላት ትኩረቱን አድርጎ ከሚሰራው "ዘ ሄግ ኢንስቲቱዩት ፎር ኢኖቬሽን ኦፍ ሎው " ከተባለ ድርጅት ጋራ በመተባበር የተሰጠው ነው፡፡