2ኛው የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቐለ ተጀመረ

ሁለተኛው የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቐለ መካሄድ ጀመሯል፡፡

ፌስቲቫሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በተገኙበት ነው የተከፈተው፡፡

የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል የክልሉን ህዝብ ከድህነት ለማላቀቅ በሚያስችል ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚካሄድ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የመክፈቻ ስነ ስርዓት የፌስቲባሉ አካል የሆነ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር በደብረፂዮን ተከፍቷል፡፡

የትግራይ አለም አቀፍ ዳይስፖራ ፌስቲቫል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡