በኳታር ዶሃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

በኳታር ዶሃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ።

በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ግድቡ ግንባታ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ትናንት ተካሂዷል፡፡

በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ሌሎች ድጋፎችን ሳይጨምር ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ይሁን እንጅ በግድቡ ላይ ተከስቶ በነበረው የቴክኒክ፣ የአስተዳደርና ሌሎች ችግሮች ምክንያት ድጋፋቸው ተቀዛቅዞ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ተከትሎ ደግሞ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ግድቡ ግንባታ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ትናንት ሐምሌ 26/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኢምባሲ አዘጋጅነት ተካሂዷል።

ተሳታፊዎችም ሁሉም ዜጋ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጥ በአዲስ ሞራል የአገራዊ አንድነት ምልክት የሆነውን የሕዳሴ ግድብ ተረባርቦ ከፍጻሜ ማድረስ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸወኘ ከኳታር የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው።