የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሀይማኖት ተቋማት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ስለሚኖራቸው አስተዋፅኦ ምክክር አድርጓል፡፡
በምክክሩ ላይ የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት ተሳትፈዋል፡፡
ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ትስስር፣ ሙስና፣ እና ሌሎች ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲከሰቱ ምክንያት እነደሆኑ ነው የሃይማኖት መሪዎቹ ገለጹት፡፡
በመድረኩም ተቋሙን ያቋቋሙት ሰባቱ የሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸወ ስላለው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውይይት አድርገዋል፡፡
ሰኞ ሐምሌ 30 የጀመረው መድረኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የተመለከተ ሲሆን ነሐሴ 1 ደግሞ የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረትን፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮፕያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሰላም ሚኒስትር የሃይማኖት እና የእምነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ጌታዋ ደስታ መንግስት የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሆነ በመግለፅ የሃይማኖት ተቋማትም በውስጣቸው ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ የበኩላቸውን ሊወጡ እንሚገባ ገልፀዋል፡፡
የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲን ህብረት፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት መሪዎች እንደገለጹት ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ትስስር፣ ሙስና፣ እና ሌሎች ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲከሰቱ ምክንያት እነደሆኑ ነው የገለጹት፡፡
በቀጣይም የሚታዩትን ችግሮችን ለማስወገድ የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ አመላካች መሆኑን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹ ትልልቅ የሃይማኖት መሪዎች ምእመናንን በሚያስተምሩት ልክ መሆን እነደሚገባቸው ነው የገለፁት፡፡
መድረኩ እስከ ነሐሴ 3 ድረስ ሚቆይ ሲሆን ነሐሴ 2 ቀን የእስልምና ጉዳዮች፣ ነሐሴ 3 ደግሞ የኢ/ያ ካቶሊካት ቤተክርስቲየን እና የኢ/ያ 7 ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የውስጥ የመልካም አስተዳደር ይዞታቸውን የሚገመግሙ ይሆናል፡፡