የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጠ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ አረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጥቷል፡፡

የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች የአረጋዊያኑን መርጃ ማዕከል  በጎብኙበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ እንዳሉት መርጃ ማዕከሉ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ዘላቂ የመድህን ዋስትና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡

ማዕከሉ ለሚያስገነባው ሆስፒታል፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች የሚሆን 155 ሚሊየን ብር የሚደርስ የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን መስጠቱን አቶ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በፊትም ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የተለያዩ ድጋፎችንና የመድህን ሽፋን መስጠቱ ይታወሳል፡፡