የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የጎዳና ኑሮና ልመናን በህግ እስከመከልከል የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ታከለ ኡማ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካደ ባለው “ያገባኛል ይመለከተኛል” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ነው ይህን ያሉት፡፡

ምክትል ከንቲባው በአዲስ አበባ ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መጥቶ ሰርቶ መኖር ይቻላል፣ ጎዳና ግን መኖርም ሆነ መለመን የማይቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ለመስራት እንገደዳለን ብለዋል፡፡

በተናጠል ከምንሰጥ መንግስት በዘረጋው አሰራር ስር በመስጠት ጎዳና ላይ የወጡ ወገኖችን በዘላቂነት መቀየር እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡

የኮንሰርቱ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ሊደርስ ፌሎውሺፕ በበኩሉ 100 ሚሊየን ብር አሰባስቦ ለትረስት ፈንዱ ገቢ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የፌሎውሺፑ ሊቀመንበር ሐዋሪያው ጳውሎስ ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመዝሙር ኮንሰርቱ ገቢ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎችን ለማንሳት የተመሰረተውን ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ለመደገፍ ይውላል ተብሏል፡፡

በስነ ስርዓቱ ከመግቢያ ክፍያ በተጨማሪ በ6400 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መካሄዱን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡