የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ ይሆናል

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በዘንድሮዉ ፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች ቁጥር በአጠቃላይ 319ሺህ 264 ሲሆን ፤ከነዚህ ዉስጥ 180ሺህ625 ወንደችና ቀሪዎቹ ደግሞ ሴቶች መሆናቸዉን ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

3453 ተማሪዎች በተለያየ ምክንያት ፈተናዉን አለመዉሰዳቸዉ ታዉቋል፡፡

ከአጠቃላይ ተፈታኞች 48.59 ፐርሰንት የሚሆኑት ፈተናዉን ከግማሽ በላይ ያመጡ ሲሆን፤ አንድ ተማሪ ከአማራ ክልል 645 ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ዉጤት አስመዝግቧል፡፡