ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሳተፉበት የጽዳት ዘመቻ በአርሲ ዞን ኢተያ ከተማ ተካሄደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የሚካሄደውን አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ኢተያ ከተማ በመገኘት አከናውነዋል፡፡

የጽዳት ዘመቻው የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

ከጽዳት ዘመቻው ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካናቸው ጋር በመሆን በአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ሙኔሳ አካባቢዎች የኩታ ገጠም ግብርናን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻው ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ  አካባቢዎች ተካሂደዋል፡፡ (ምንጭ:-ኢዜአ)