ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመቐለ እየተከበረ በሚገኘው የአሸንዳ በዓል ላይ ተገኙ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአሸንዳ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በዛሬው ዕለት  መቐለ ገብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በትግራይ ክልል ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልና በሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የአሸንዳ   በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰላም፣ አንድነትና ልማት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በትግራይ ክልል በነሃሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ፣ ማሪያ እና ዓይኒ-ዋሪ በዓላት የክልሉን ባህል፣ ትውፊትና የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡