ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣዉን ዝቃጭ በአግባቡ ለማስወገድ የሚያስችል መመሪያ ይፋ ተደረገ

ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪዎቿ የሚወጣዉን በካይ ፈሳሽ ወይም ዝቃጭ በአግባቡ ለማስወገድ የሚያስችል መመሪያ ዛሬ ይፋ አደረገች፡፡

መመሪያዉ ለ3 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የቆየ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

መመሪያዉን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ እንደገለፁት ከሆነ ይህ መመሪያ ሀገሪቱ እስከዛሬ በዘርፉ ያወጣቻቸዉን ፖሊሰዎች በአግባቡ ለመፈፀም ያስችላል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለም በዘርፉ የሚከናወነዉ ስራ ባለቤትንና ተጠያቂነትን  በግልፅ ያስቀምጣል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን በበኩሉ ከዚህ በፊት የነበሩ ኢንዱስትሪዎችም ሆኑ እንደ አዲስ የሚቋቋሙት እየለቀቁት ያለዉ ዝቃጭ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ገልፆ ይህ መመሪያ በዘርፉ የሚከናዉኑትን ስራ ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችል ተናግሯል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለሊሴ ነሜ መመሪያዉ ከቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጀመር በሀሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡