የካንሰር ህመምን ለመከላከል በሚከናወነው ስራ የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ

የካንሰር ህመምን ለመከላከል በሚከናወነው ስራ የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡

በአፍሪካ የካንሰር ህመም ላይ የሚመክር አህጉራዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በአፍሪካ የካንሰር ህመም ከግንባር ቀደም ገዳይ በሽታዎች ተርታ መሆኑ በወርክሾፑ ላይ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ችግሩን ለመከላከል ሀገራቱ የበለጠ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገራት ለውጦች እየታዩ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባና ስራውንም በቴክኖሎጂ ማገዝ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ኢትዮጵያ ድምፅ አልባ ለሆነው የካንሰር ህመም ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ ተናግረው፣ ኢትዮጵያ በትንባሆና በአልኮል መጠጦች ላይ ያወጣቻቸውንና የጣለቻቸውን ገደብ ጠቁመዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም ተጨማሪ መሰል ገደቦችን የሚጥሉ መሰል ህጎች ይወጣሉ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ስራውን በቴክኖሎጂ የማገዝና ቅድመ መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ፡፡