ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ውጤት ኖሯቸው ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ልትሰጥ ነው

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ውጤት ከ8ኛ ወደ ዘጠነኛ ለሚያልፉና ከፍለው መማር ለማይችሉ በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች በነፃ የመማር እድልን ለመስጠት ቃል ገባች።

የነፃ የትምህርት እድሉ በቤተክርስያኒቷ ስር በሚተዳደሩ ት/ቤቶች የሚሰጥ ይሆናል።

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ላይ እየሰራ ያለውን ስራ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደምትደግፈው ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ሱራፌል ተናግረዋል።

የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያናት ሊቀ-ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ኢ/ር ታከለ ኡማ ቫቲካንን እንዲጎበኙ የላኩትን ጥሪ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ለከንቲባው አቅርበዋል።

ኢ/ር ታከለ በፖፕ ፍራንሲስ የቀረበላቸውን የቫቲካን ጉብኝት ጥሪ በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ካርዲናሉ ከከተማ ልማት ጋር የተገናኙ መፅሐፍትን በስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ አበርክተዋል፡፡

(ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት)