በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት አመራሮች የፍትህ ቀንን ማክበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት አመራሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜ 5፤ በክልል ደረጃ ጳጉሜ 3 የሚከበረውን የፍትህ ቀንን ምክንያት በማድረግ በ2011 በጀት አመት የተከናወኑ ስራዎችንና በቀጣይ የፍትህ ቀንን ማክበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

አመራሮቹ ባለፈው በጀት አመት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን የገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይ ጳጉሜ ሶስት ላይ የፍትህ ወር መዝጊያ ስነስርዓት ከክልሉ ህዝብ ጋር በመሆን በተለያዩ ውይይቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል፡፡

በዘርፉ የተከናወኑ ሪፖርሞች አመርቂ መሆናቸውም በውይይቱ የተነሳ ሲሆን፣ የተሰሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በ2012 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

በውይይቱ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ፍትህ ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡