ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ የስርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናት ጉባኤ ተጀመረ

የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታ አካል የሆነው ይህ ጉባኤ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ የሀገሪቱን ስርዓተ ትምህርት ለማሻሻል ጠቃሚ ግብዓት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት በተካሄደው ጥናት በ2001 ዓ.ም የተከለሰው አጠቃላይ ስርዓተ ትምህርት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመፈተሽ ያስቻለ እንደነበር የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ፂዮን ተክሉ ገልፀዋል፡፡

ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ስኬታማነት እና ተማሪዎች በእውቀትና ክህሎት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅ መሆን እንዳለበትም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የተናገሩት፡፡

የስርዓተ ትምህርቱ ጥናት ነፃ እና ገለልተኛ በሆነ አካል እየተካሄደ እንደሚገኝና በዚህም የተሻሉ ግብዓቶች እንደተገኙበትም በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡

ሶስት ዓመታት የሚሸፍነው የስርዓተ ትምህርት ጥናቱ  አሁን ላይ የአንድ ዓመቱን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

መድረኩን የትምህርት ሚኒስቴር በተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ድጋፍ  ያዘጋጀው ሲሆን፤ ጥናቱን ያካሄደው ደግሞ ካምብሪጅ አሰስመንት ኢንተርናሽናል የተሰኘ ተቋም ነው፡፡