ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ማዕከልን ጎበኙ

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የልብ ማዕከል ጎበኙ፡፡

በማዕከሉ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ልጆችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግም ለልጀቹ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

ከተመሰረተ አስር አመታት ገደማ የሆነው ማዕከል እስካሁን ድረስ ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልጆች ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

ማዕከሉ የሚያደርጋቸው የስራ እንቅስቃሴዎች የሚያስደስቱ መሆናቸውን ያመለከቱት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ምን አይነት ታላቅ ስራ መስራት እንደምንችል ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ:- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት