ኢትዮጵያና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት/ዩኤስ አይ ዲ/ የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ለቀጣይ 5 ዓመት የሚቆየውን አዲስ ስምምነትን በዩኤስ አይ ዲ በኩል ነው የተፈራረመው ።

ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ዩ ኤስ አይ ዲ ዓለም ላይ የቲቢ በሽታን ለማጥፋት የሚተገብረው ፕሮግራም አካል ሲሆን በ2035 የቲቢ በሸታን ለመጥፋት "ግሎባል አክስሌተር ቱ ኢንድ ቲቢ" በሚል መርህ እየተሰራ ይገኛል ።

በተጨማሪም ስምምነቱ እ.አ.አ በ2022 ዓለም ላይ ለ40 ሚሊየን የበሽታው ተጠቂዎች ህክምና ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ላይ የቲቢ በሽታን ለማጥፋት በትብብር  እየሰራ ከሚገኝባቸው 30 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡