የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

ሀገር አቀፉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ይፋ በተደረገው ውጤት መሰረት ከተፈታኞቹ መካከል ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ ማምጣታቸው ታውቋል።

75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች ደግሞ ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ እንዳመጡ ነው የተገለጸው።

ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የዘንድሮውን የ10ኛ ክፍል ፈተና መፈተናቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ http://app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።